ኢትዮጵያን እናገልግል ጳግሜ 1/2015 ዓ.ም. አዲስ አበባ
የኢትዮጵያን ስኬቶች በማጉላት፣ካጋጠሙን ፈተናዎች ፣ለወደፊቱ ትምህርት መውሰድ በሚገባን መንገድ ላይ ሃገራዊ ተግባቦት በመፍጠር በተለያዩ ዝግጅቶች እያንዳንዱን ቀን እንዲታሰብ እንደ አገር ተወስኗል፡፡
ከዚህም ጋር በተያያዘ ጳግሜ 1 የአገልግሎት ቀን ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፣"ኢትዮጵያን እናገልግል" በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ ሃገርን ማገልገልና ህዝብን ማገልገል ምን ማለት እንደሆነ በመግለጽ፣በአገልግሎት ላይ ያጋጠሙ ፈተናዎችና መፍትሄዎቻቸው በመነገር፣የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት መደረግ ስላለባቸው ነገሮች አዳዲስ ሃሳቦች በማቅረብ፣ከአገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ የሚጠበቁ ነገሮች የሚነገሩበት ለቅን አገልጋዮች ምስጋና የሚቀርብበት ቀን በመሆን ተከብሮ ይውላል፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም እንደ አገር ከሌሎች ተቋማት ጋር ማለትም ትራንስፖርት ሚኒስቴር፣የጤና ሚኒስቴር፣የግብርና ሚኒስቴር፣የቱሪዝም ሚኒስቴር፣የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ዕለቱን ከማክበር ባሻገር እንደተቋምም ከኮሚሽኑ ሠራተኞች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የፓናል ውይይት በማካሄድ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ደም በመለገስ ተከብሮ ውሏል፡፡