ስለኛ

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ ሲቪል ሰርቪስ በጥቅምት 14/1900 .. ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ስድስት ሚኒስትሮችን በመሾም እንደ ተጀመረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ የመንግሥት ሰራተኞች አስተዳደር ለማዘመን የነበረውን መዋቅር መለወጥ በማስፈለጉ በትዕዛዝ ቁጥር 23/54 “ጠቅላይ መስሪያ ቤትየሚባል ተቋም (እንደተሻሻለው) በህግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 269/55 በይፋ ስራ ጀመረ፡፡ በዚሁ መጠሪያ እስከ 1967 .. ሲጠራ ከቆየ በኋላ ማዕክላዊነቱን እንደጠበቀየመንግሥት ሰራተኞችና መስሪያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽንበሚል በአዲስ ድርጅታዊ መዋቅር ተደራጅቶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ 

ከደርግ ውድቀትና የሥርዓት ለውጥ በኋላ የሽግግር መንግስቱ ሲመሠረት የማዕከልና የክልል አስፈፃሚ /ቤቶችን ሥልጣንና ኃላፊነት ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 41/88 የኮሚሽኑ ሥልጣንና ኃላፊነት በአዲስ መልክ ተደነገገ፡፡ ከሽግግር መንግሥቱ በኋላ የኢ.... አስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 256/94 ደግሞየሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲበመባል ተጠሪነቱ ለአቅም ግንባታ ሚኒስትር ተደርጎ ተቋቋመ፡፡

በመቀጠልም በአዋጅ ቁጥር 691/2003 መሠረት የአቅም ግንባታ ሚኒስቴርና የሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ በመዋሀዳቸውየሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴርበሚል ስያሜ 2003 . መቋቋሙ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ስያሜውን እንደያዘ የተሰጡትን ተግባራትና ኃላፊነቶች እስከ 2008 . ሲወጣ ከቆየ በኋላ አገሪቷ በደረሰችበት የዕድገት ደረጃ ልክ  አገልግሎቱን በመንግስትና በግል ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ፣ የሰው ሀብት ልማትን፣ ተቋማዊ ለውጥን እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማስተባበርና ለመከታተል እንዲያስችል በአዋጅ ቁጥር 916/2008 “የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴርተብሎ እንደገና ተዋቀረ፡፡

በመጨረሻም መንግሥት በያዘው አገራዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል አንዱ በመሆኑ የአስፈጻሚ ተቋማትን አደረጃጀትና አሰራር በማዘመን ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የተጀመረውን አገራዊ ለውጥ እውን ለማድረግ የመንግሥት ተቋማትን አደረጃጀትና አሰራር መፈተሽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንበመባል በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡ በዚሁም መሠረት የሲቪል ሰርቪስ ዘርፍን የሰው ሀብት ልማትና የሥራ አመራርን፣ የመንግሥት አስፈጻሚ ተቋማትን አቅም የመገንባት፣ የአገልግሎት አሰጣጥንና የቅሬታና አቤቱታ ሥርዓትን የመዘርጋት እና የሥራ አካባቢ ምቹነትን የማረጋገጥ፣ የማስተባበር እና የማስተግበር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ 2014 . ደግሞ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 42(2) መሠረት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ስልጣን፣ ተግባርና አደረጃጀት ለመወሰን በጸደቀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 502/2014 የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ይወጣል፡፡

 

ተልዕኮ

የመንግስት ተቋማት በአዋጅ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በቅልጥፍናና በውጤታማነት በመወጣት ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን በብቃት ማሳካት እንዲችሉ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ስራዎችን በብቃት መምራት፣የለውጥና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ፕሮግራሞች በውጤታማነት እንዲተገበሩ በመደገፍ፣ በመከታተል፣ በማስተባበርና በመቆጣጠር ህዝብንና ዜጋን የሚያገለግል ጠንካራና ውጤታማ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡

ራዕይ

አገልግሎቶች በውጤታማነት የሚያቀርቡ ተቋማትና በገነቡት መልካም እሴት የተመሰገኑ የመንግሥት ሠራተኞች ካሏቸው አምስት የአፍሪካ ሀገራት መካከል 2022 .. ኢትዮጵያ አንዷ ሆና ማየት።

ግቦች

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ስትራቴጂያዊ ግቦች

1. ነፃና ገለልተኛ የሠራተኛ ስምሪትና መንግስታዊ ሥርዓት መገንባት፣ [የአስተዳደር ፍርድ ቤት እና የኢንስፔክሽን]

2. የተዋጣለት የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አደረጃጀትና የሥራ ምዘና ሥርዓት ግንባታ ማሳለጥ፣ [value

for money: JEG]

3. የመልካም ሥራ ባህልና የዕሴት ግንባታ ማፋጠን፣ (Behaviour: Core Competency)

4. ቀልጣፋና ውጢታማ የአመራርና የፕሮፌሽናል ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋት፣ (Techincal competency)

5. ዘመናዊና ጥራት ያለው የአገልግሎት አቅርቦት ሥርዓት ማላቅና ማፅናት (value for taxpayers’ money and

commercial outcomes)

6. የሥራ አፈፃፀም ምዘና ከተቋም ውጤት (Delivering valuable services for money) እንዲሁም ከማትጊያ (Reward)

ጋር ማጋመድ፣

7. የኢ-ሲቪል ሰርቪስ አቅርቦት ሥርዓት ግንባታ ማፋጠን፣

ዋና እሴቶች

እሴቶች

1. አገልጋይነት

2. ነፃና ገለልተኝነት (Impartiality & Objectivity)

3. እውነተኛነትና ልህቀት (Honest & Excellence)

4. ተባባሪነት (Collaborating and partnering)

5. ቅልጥፍናና ውጤታማነት (Efficiency & Productivity for market construction)

ተግባራት እና ኃላፊነቶች

 • በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት መስሪያቤቶች የሰው ሀብት ልማት በቀጣይነት የሚለማበትንና ጥቅም ላይ የሚውልበትን ስልት ይቀይሳል፤
 • የመንግሥት ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ በቀጣይነት የሚሻሻልበትን ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የመንግሥት ዘርፍ አቅም ግንባታ ሥራዎችን ያስተባብራል፤
 • የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ምልመላና መረጣ በብቃት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርጋል፤
 • ብቃት ያለውና ውጤታማ አመራርና ሲቪል ሰርቪስ እንዲገነባ ስልት ይቀይሳል፤ የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
 • በሲቪል ሰርቪሱ በብቃትና በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የክፍያና የማበረታቻ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤ ውጤታማነቱን ይገመግማል፤ አስፈላጊውን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፡፡
 • የፌዴራል የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አስተዳደር ህጎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ የሠራተኞች ሥነ-ምግባር መከታተያ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤ የአተገባበሩን ውጤታማነት ያረጋግጣል፡፡        
 • የፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችን የውስጥ አደረጃጀት አግባብነት መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፤ በአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናት ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤ የፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችን የስልጣንና ተግባራት ወሰን አወቃቀርና አደረጃጀት በተመለከተ ጥናት በማካሄድ ለመንግስት የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤
 • በፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል
 • የሲቪል ሰርቪሱ የሰው ሀብት አመራር መረጃዎችን ሥርዓት ወጥነት እንዲዳብርና እንዲተገበር ያደርጋል፤ ማዕከላዊ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል
 • በህግ መሠረት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ  ሠራተኞችን ከጡረታ እድሜ ክልል በላይ በአገልግሎት ላይ ስለማቆየት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፤
 • በመንግስት    ሠራተኞች ህግ መሠረት በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች በሚቀርቡ ይግባኝ ላይ የፍሬ ነገር የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፤