የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደም የመለገስ መርሀ-ግብር አከናወነ

መስከረም 3/2015 ዓ.ም.አዲስ አበባ፣ ጥፋትና ጦርነት ተፈጥሯዊ ባህሪው የሆነው አሸባሪው ህውሓት ለሰላም የተዘጋጀውን እጅ በመንከስ የሰላም አማራጩን አፍርሶ እና የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡና ኢትዮጵያውያንን የሰላም አመራጭ ልመና እረግጦ ለ3ኛ ጊዜ ጦርነት ማወጁ ይታወሳል። በመሆኑም ኮሚሽኑ ሠራዊታችን ይህን አሸባሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ለሚያደርገው የህልውና ዘመቻ ያለውን አጋርነትና ድጋፍ ለመግለፅ ከኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ ደም የመለገስ መርሃ-ግብር አከናውኗል፡፡

Share this Post