የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከክልሎችና ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም የውይይት መድረክ አካሂዷል
ይህን የተናገሩት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊዎች ጋር በተደረገው የ6 ወር እቅድ አፈፃጸም ውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
አክለውም ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ከገባበት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ለማውጣትና ሪፎርም ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን ሌት ተቀን እየሰራን መሆኑ ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል ብለዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው ከፖሊሲ ቀረፃ ጀምሮ በርካታ የህግ ማእቀፎችና ፖሊሲ ማስተግበሪያ እስትራቴጂዎች ዝግጅት መደረጉና፣አዳዲስ መዋቅሮች በፊዴራል መስሪያ ቤቶችና በራሱም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ክልሎች በኛ በኩል የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ዎችን በተመለከተ መልስ ያልተሰጠባቸው ሥራዎች ጠረጴዛ ላይ እንደሌሉ፣ በርካታ ጥናቶች አስጠንተን የጨረስን መሆኑንና ከዚህ በኋላ የሚቀረው ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች አፀድቀን ወደ ሥራ መግባት ብቻ መሆኑን በመገንዘብ በፍጥነት ወደ ስራ ሊያስገባችሁ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ልታደርጉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ኮሚሽነሩ የጥበቃ ፣የፅዳት፣ ተላላኪ ዝቅተኛ መደቦች እጃቸው ላይ የሚገባው ትንሹ ወራሀዊ ደሞዝ 900 ብር እንደሆነና አንድ ዳቦ 12 ብር መግባቱን ገልጸው፤ እዚህ ላይ ለኛ ማንም ማብራሪያ ሊሰጠን አይችልም፤ ነገር ግን እኛ በእጃችን ላይ ዲያመንድና ወርቅ ይዘን ነው ሌላ የምንጠብቀው፣ ሰለሆነም ሁላችንም መጀመሪያ ወደ ስራ እንግባ በስርዓቱ አገልግሎትን እንስጥ፣ በሥርዓቱ ግብር እንሰብስብ፣ መሬት ለሚፈልግ፣ ማልማት ለሚፈልግ፣ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልግ ሳናጉላላ እናስተናግደው ፤ ይህ ነው በእጃችን ላይ ያለው ውዱ ነገር !!! ይህ ሲሆን በፍጥነት እንለወጣለን ብለዋል፡፡
በመድረኩም የክልሎች ከ6ወር አፈጻጸም በተጨማሪ የሲቪል ሰርቪስ ፖሊሲን ለማዳበር የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ጥናት እና የተገልጋይ የእርካታ ጥናት ቀርቦ በጥናቶቹ ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ መድረኩ የሲቪልሰርቪስ ኮሚሽን ከUKAID እና UNDP ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው፡፡