"የመንግስት ሰራተኞች ተግባብተንና ተባብረን ለጋራ ኣላማ በመስራት አገራችንን ብሎም ሲቪል ሰርቪሱን ወደ ተራራው ጫፍ ልናወጣ ይገባል!"

አዲስ አበባ ሐምሌ21/11/14 ዓ.ም

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን "ኢትዮጵያ ታመስግን!" በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን ብሄራዊ መርሃ-ግብር አካሄደ

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን "ኢትዮጵያ ታመስግን"! በሚል መሪ ቃል በአገር ደረጃ የተዘጋጀውን ብሄራዊ መርሃ-ግብር ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በመሆን በጋራ ያከናወነ ሲሆን በመድረኩ ስላለፍነው መልካምና መጥፎ አጋጣሚዎች፣ወደፊት ስለሚታዩ ብሩህ ተስፋዎች የኢትዮጵያን አምላክ የማመስገን ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡

እንዲሁም በወቅታዊ የአገራዊ ፈተናዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በኩል ገለጻ ተደርጓል፡፡

Share this Post