ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተደረገ
ለጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ተጠሪ ከሆኑት ተቋማት አንዱ የሆነው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በገንዘብ ከ 2ሚሊዮን ብር በላይ በአይነት ደግሞ ከ 500 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የምግብ ግብአቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በአይነት ከ 1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በአጠቃላይ ከሁለቱ ተቋማት በገንዘብና በአይነት ከ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አሰባስበው ለኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስረክበዋል።
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከ 2 ሚሊዮን 900 ሺህ ብር በላይ አሰባስቦ ግንባር ድረስ በመሄድ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።
የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ለዊጂ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለፁት ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ሰራዊታችን በየግንባሩ ለሀገሩ እየተዋደቀ እኛ በቻልነው አቅም ከጎኑ ልንቆም ይገባል ብላችሁ አጋርነታችሁን በተግባር በማሳየታችሁ ቅልቅ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ አያይዘውም ይህ ድጋፍ ለሰራዊቱ ትልቅ የሞራል ስንቅ በመሆኑ አጋርነታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አደራ እላለሁ ሲሉ ተናግረዋል።