17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል

በመድረኩም የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር የሆኑት ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በዓሉን ስናከብር ከህብረ-ብሄራዊነት ጋር በተያያዘ በምናገኛቸው መድረኮች የምንገልጻቸውን ሃሳቦች ወደ መሬት በማውረድ ወደ ተግባር መለወጥ ትልቁና ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንና ለዚህም ስኬታማነት መደማመጥ አበይት ሚና እንደሚኖረው መድረኩን በከፈቱበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ስርዓት ምንነት፣ባህሪያትና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱም ብዝሃነታችን የአገራችንን እሴቶችና አንድነት ሊያጠናክር በሚችል መልኩ ልንጠቀምበት እንደሚገባ፣ሲቪል ሰርቪሱ ብዝሃነትን ባገናዘበ መልኩ ማጠናከር ተገቢ እንደሆነና በአጠቃላይም እንደአገር የተቋቋመው የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽንም አገራዊ መግባባትና ሰላም እንዲረጋገጥ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Share this Post