የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከፌዴራል ዋና ኦዲተር ጋር በመተባበር ለአራተኛ ጊዜ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ -ግብር በአዲስ አበባ አይ ሲቲ ፓርክ /ICT PARK/ ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. መላው ሰራተኛ በተገኘበት የተለያዩ ከ13 አይነት በላይ አገር በቀል ችግኞችን አብካዶና ማንጎ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች በአጠቃላይ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ ችግኞችን ተክሏል፡፡
በችግኝ ተከላው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የኮሚሽነር ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አልማው መንግስት እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንደ አገር ባዘጋጁት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በየአመቱ በመትክላችን በርካታ ጥቅሞችን እያገኘን እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በተለይ አፈር መሸርሸር ፣ከፀሀይ ሀሩር እና ከበረሀማነት ወደ የተስተካከለ ንፁህ አየር አገራችን ወደ መቀየር ደረጃ አድርሷታል ብለዋል፡፡
አክለውም በዚህ መርሀ ግብር የተለያዩ አገር በቀል ችግኞችና ፍራፍሬዎች በመተከላቸው ወደ ፊት አገራችን ፍራፍሬ ወደ ውጪ የሚላክበት ሰፊ እድል እናዳላት ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ሰላሌ ዞን ውጫሌ ወረዳ በኢፋ ሰላሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ "ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት" አረንጓዴ አሻራ -መርሐ ግብር እንዲሁም የፌዴራል ዋና ኦዲተርና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በጋራ በመሆን "በሆለታ" ከተማ “ልዩ ስሙ "ቡርቃ ሃርቡ" በተባለ አካባቢ አረንጓዴ አሻራ መርሐ -ግብር አካሂደዋል ብለዋል፡፡