የሲቪል ሰርቪሱን ቀጣይ ስራዎች በተመለከተ ከአለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

የሲቪል ሰርቪሱን ቀጣይ ስራዎች በተመለከተ ከአለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ *****************************************************************   የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቀጣይነት በሚሰራቸው ስራዎች ዙሪያ በኢትዮጵያ ከUNDP አመራሮች ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን በጋራ ውይይቱ ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) ሲቪል ሰርቪሱ ዘረፍ በቀጣይነት ሰለሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ኮሚሽነሩ በገለጻቸው ሲቪል ሰርቪሱ በተለያየ መንገድ ለውጥ እንዲያመጣ የአለም አቀፍ አጋር አካላት ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸው UNDPም እንደ አንድ አጋር አካል በተለያዩ ድጋፎች ኮሚሽኑን እንዲያግዝ ጠይቀዋል፡፡ በውይይቱ በኢትዮጵያ የUNDP ዋና ዳይሬክተር ቱህራን ሳልህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስን ቀጣይነት ባለው መልኩ በተለያዩ ጉዳዮች ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Share this Post