በመንግስት ሠራተኞች የቅጥር እና ደረጃ እድገት የብቃት ምዘና ስትራቴጂ ላይ ምክክር ተካሄደ

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ እንደተናገሩት ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው ምክክር መድረክ ከዚህ ቀደም ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም.በቢሾፍቱ መካሄዱን አስታውሰው፤ይህንን ተከትሎ በረቂቅ ማዕቀፉ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች በሰነዱ መካተታቸውን ለማሳየት፣መድረኮች ላይ የሚነሱ ሀሳቦች ምን ያህል ገንቢ እንደሆኑ እንደምናምን፣አክብሮታችንን ጭምር ለማሳየትና ሰነዱ ላይ ተጨማሪ አስተያየት እንዲሰጥበት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

በማስከተልም የመንግስት ሠራተኞች የቅጥር እና ደረጃ እድገት የብቃት ምዘና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ በአቶ ተስፋዬ አጥሬ የፕሮጀክት ፅ/ቤት ም/ኃላፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡

በመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በዋናነት እንደዚህ አይነት መድረኮች እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆኑና አንድ ሰነድ ታትሞ ህግ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት በርካታ የምሁራን፣ የባለድርሻ አካላት ውይይት እንደሚያስፈልግ በዚህም ሲቪል ሰርቪስ እያደረገ ያለው አገር የማዳን ሥራ ሊበረታታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በቢሾፍቱ ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በመንግስት ሠራተኞች የቅጥር እና ደረጃ እድገት የብቃት ምዘና ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ በተሰጠው ግብዓት መሰረት ኮሚቴ ሆነው ሰነዱን ለማዳበር የተሳፉ አካላት የምስጋና የምሥክር ወረቀት በዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ተበርክቶላቸዋል፡፡

Share this Post