የዓለም ህፃናት፣የኤች አይ ቪ ኤድስ ፣የፀረ ፆታ ጥቃት እና የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ቤላ ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አደረገ
በቦታው ላይ ተገኝተው ስጦታውን ያበረከቱት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክብርት ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት በቅድሚያ የማዕከሉን መስራች አቶ ቢንያም በለጠን በማመስገን የማእከሉ መሪ ቃል "ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው" የሚለውን ኖሮ ያሳየን ታላቅና ለብዙዎቻችን አርአያ የሆነ ሰው መሆኑን ገልጸዋል።
በማእከሉ ከ7500 በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችን ትላንት በተለያየ የስራ መስክ አገራቸውንና ህዝባቸውን ሲያገለገሉ የነበሩ ሲሆኑ ዛሬ በጤና እጦት፣ በእርጅና፣በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው የኛን ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን አለሁ ልንላቸው ይገባል ብለዋል።ኢትዮጲያውን መልካም የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል ያለን ህዝቦች በመሆናችን ልዩ ልዩ በአላትን ምክንያት በማድረግ ወገኖቻችንን ልንደግፍ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም ይህንን ቅዱስ አላማ ለማስፋፋት 70 በመቶ የተጠናቀቀውን የማእከሉን ህንፃ እንዲያልቅ ሁላችንም በግል፣ በመስሪያ ቤት፣ በድርጅት የበኩላችንን ድጋፍ በማድረግ አረጋዊያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን እንደግፍ በማለት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በመጨረሻም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።