አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣2017
ዛሬ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አካሂዷል፡፡
በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመሠረታዊነት ለመፍታት የተጀመረው ሪፎርምን መሠረት በማድረግ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ የመጀመሪያውን ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ስራዎችን በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ ስምንት ተቋማት በተገኙበት ገምግሟል፡፡
ተቋማት ያከናወኗቸውን ተግባራት በዝርዝር በመቃኘት ጥንካሬዎችን፣ውስንነቶችን በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በቀጣይም መልካም ጅምሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል በሪፎርሙ የታቀፉ ተቋማት ያላቸውን ልምዶች የሚቀያየሩበት አውድ መፍጠር መቻሉ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ ተጠቁሟል፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችንም የሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴው ጎብኝቷል፡፡